የቤ/ጉ/ክ/መ ስራና ክህሎት ቢሮ ከቆላማ አከባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የጋራ ፍላጎት ላላቸው ቡድን ስሰጥ የቆየውን የረጂም ጊዜ ስልጠና ተጠናቆ ዛሬ ተመርቀዋል ።
***********************
የቤ/ጉ/ክ/መ ስራና ክህሎት ቢሮ ከቆላማ አከባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የጋራ ፍላጎት ላላቸው ቡድን ስሰጥ የቆየውን የረጂም ጊዜ ስልጠና ተጠናቆ ዛሬ ለምርቃት በቅተዋል ።
(ግንቦት) ፤ 08/09/2016 ዓም ስራና ክህሎት ቢሮ ከቆላማ አከባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ላይ ለጋራ ፍላጎት ላላቸው ቡድን በእህል እና በወርቅ ወፍጮ ኦፕሬተርነት የሰለጠኑ ሠልጣኞችን የምርቃት ፕሮግራም አካሂደዋል ።
ሠልጣኞቹ በሰለጠኑት የሙያ መስክ በአሁኑ ሰዓት የሚስተዋለውን ዳካማ የስራ ባህልን ለማስወገድ ላሌሎች ተምሳሌት መሆን ይጠበቅባቸዋል ስሉ ምክረ ሀሳብ በመለገስ ንግግር ያደረጉ የስራና ክህሎት ቢሮ የክህሎትና ተቋማት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃፈር ሀሩን ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል ።
ተመራቂዎቹ ከተለያዩ ወረዳዎች ተመልምለው በእህል እና በወርቅ ወፍጮ ኦፕሬተርነት የተሠጣቸው ስልጠና በቂ እውቀት እና ክህልን የቀሰሙበት እንደሆነ በመጥቀስ የሚጠበቅባቸውን መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
በክልሉ የቆላማ አከባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተውፊቅ አብዱልቀዩም በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ሰልጣኞች በቁርጠኝነት ወደ ስራ መግባት እንዲችሉ የፕሮጀክቱ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጥቀስ የተጣለባቸውን ሙያዊ ሀላፊነት ለመወጣት የቃለ መሃላ ስነ – ስረአት በመፈጸም ባለድርሻ አካላትም ለስራ አጥ ወጣቶች የሚጠበቀውን ሁሉ ትብብር ማድረግ እንደሚገባም ጠይቀዋል ።
በመጨረሻም በኮሌጁ ግቢ የታዩት የመልካም ለውጥ ውጤት የሆኑት አንዳንድ የስልጠና ማዕከላትን በመጎበኘትና ምልከታ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።




All reactions:
15Endris Ali and 14 others