(አሶሳ፤ ሐምሌ 09/2016 ዓ/ም) በኮሌጁ አመራሮች ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የ12 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የጥቅል ሪፖርት ግምገማ መድረክ እያካሄደ ይገኛል::
የኮሌጁ ዲን አቶ ተመስጌን ሀይሉ በሪፖርት መድረክ ግምገማ ወቅት እንደተናገሩት የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በቴክኖሎጅ ሽግግር ዘርፍ ያልተሰሩና ትኩረት የሚሹ ዕቅዶች አካተን የኮሌጁን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል::
በቀረበው ሪፖርት አፈፃፀም ላይ በጥልቀት በመገምገምና የኮሌጁ የውስጥ ገቢ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለቀጣይ በጀት ዓመት ራሳቸውን በደንብ በማዘጋጀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለባቸው ተነስቷል::
ባለፉት 2016 በጀት አመት በኮሌጁ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን በጥልቀት በመገምገም እና የ2017 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ የሚሆኑ ግበዓቶችን በመሰብሰብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል
የአፈፃፀም ሪፖርት መድረኩ ከሐምሌ 09–10/2016 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ እና ሁሉም ሰራተኛ በተገኘበት እንደሚቀጥል
ተናግረዋል
በኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት




