የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፣ በአሶሳና በካማሽ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎች የውጭ ሀገር የስራ እድል እንዲመቻችላቸው ሲሰለጥኑ የነበሩት ዜጎች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፣ በአሶሳና በካማሽ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎች የውጭ ሀገር የስራ እድል እንዲመቻችላቸው ሲሰለጥኑ የነበሩት ዜጎች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

****************************************

በምርቃት መርሀ ግብሩም በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከተማ አስተዳደሩን ጨምሮ በአሶሳና በካማሽ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች በክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት ተመልምሎ የውጭ ሀገር የስራ ዕድል ለሚመቻችላቸው 217 የሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች በአሶሳ ግብርና ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ሲሰጥ መቆየቱን በመግለፅ ስልጠናው አጫጭር እና በተግባር የታገዘ እንደነበርና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የስልጠና ሂደቱ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በንድፈ ሀሳብ ካጠናቀቁ በኋላ በተግባር የታገዘ ስልጠና ጨርሰው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC) በመውሰድ ብቁ ሆነው ቀጣይ የቪዛ ሂደቱን እንደሚጠብቁ ተገለፀ፡፡

የስራ ስምሪት ስልጠና የወሰዱት ስልጣኞችም ብቃታቸውን በማረጋገጥ ወድ ስራ ለማስማሰመራት በስራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነትና በኮሌጁ አሰልጣኞች በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ዛሬ ለመመረቅ ችለዋል።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰኔ 6/10/2016ዓ.ም የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚዩኒኬሽን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *