የአሶሳ ፓሊ ቴክኔክ ኮሌጅ ከክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ጋር በመሆን የኮሌጁን ዌቭ ሳይት አበልጽገዋል።
በኮሌጁ ከሳይንስና ቴክኖሎጅ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የተከፈተውን ዌቭ ሳይት በተመለከተ ውይይት ተደረገ።
ይህም የኮሌጁን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ጠቅላላ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲገኙ ከማድረግ ባሻገር ምቹና ቀልጣፋ የሆነ አዲስ መተግበሪያን በመጠቀም ስራ ላይ ለማዋል ሂደቱን በማገባደድ ላይ ይገኛል። ይህ መተግበሪያ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ሆኖ በቀላሉ መረጃ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ ለስራ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን የቴክኖሎጂ መፍትሄን በመጠቀም መቅረፍ እንደሚቻል በኮሌጁ አመራሮችና ማህበረሰብ በኩል ተገልጿል።
ሰኔ 05/16 ዓ/ም