በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

(ሰኔ 05/2016 አ/ም፣አሶሳ)የሴቶችን ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የውይይትና አባላትን የማጠናከሪያ መድረክ ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ አስተባባሪዎች እንደገለጹት ሁለተናዊ ልማታችንን ለማሳለጥ እና አንድነትን በማጎልበት ረገድ ሴቶች ከወትሮው በተሻለ አቅማቸውን አሟጠው እንዲሰሩ ለማድረግ ነው ያሉ ሲሆን የሴቶች ሊግ አደረጃጀት ከተዋቀረ ወዲህ ሴቶች በሰላምና ደህንነት የሀገር አንድነት እንድጠበቅ ግንባር ቀደም ተዋንያን በመሆን፣ በኢኮኖሚዉ ዘርፍ በፓርቲያችን እና በሊጉ ፅ/ቤት የሚወርዱ የተለያዩ ስምሪቶችን ቀድሞ ወደ መሬት በማዉረድ ለተቋማችን ብሎም ለክልላችን ብልፅግና ትልቅ አስተዋጽኦ ማበረከት እንችላለን ብለዋል፡፡

አክለውም የሴቶች ሊግ መዋቅር ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ያለው ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶች ተሳታፊነት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም የሴቶችን ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ይህንን አላማ ለማሳካት ሁሉም ሴቶች ከፓርቲያችን ጎን በመሰለፍ ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ እንዲያደረጉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ከዚህ በፊት የነበረውን አደረጃጀት በማጠናከር የነበሩ ክፍተቶችን ለይቶ በመቅረፍ ቀጣይ የአባላቱን ቁጥር ከፍ በማድረግ የበለጠ ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *