የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር በአሶሳ እና በካማሽ ዞን ስር ለሚገኙ ወረዳዎች የውጭ ሀገር የስራ እድል ለሚመቻችላቸው ለ206 የሚሆኑት ዜጎች አጫጭርና በተግባር የታገዘ ስልጣና እየሰጠ ይገኛል ።
****************************************
በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሶሳና በካማሽ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች በክልሉ ስራና ክሎት ቢሮ አስተባባሪነት ተመልምሎ የውጭ ሀገር የስራ ዕድል ለሚመቻችላቸው 206 የሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች እየሰጠ ያለውን አጫጭር እና በተግባር የታገዘ ስልጠና በአሶሳ ግብርና ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በተጠናከረ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል። ።
የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስትር ዜጎች ለቤት ውስጥ ስራ ህጋዊ በሆነ መንገድ ለማሰማራት ከውጭ ሀገራት ጋር በተፈጠረው ስምምነት መሠረት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሰለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት ለማፍራት እና የዜጎችን መብት፣ ክብርና ደኅንነት በማስጠበቅ በክልሉ አሶሳና ካማሽ ዞን ተመልምለው ለመጡ ዜጎች በተግባር የታገዘ አጪጭር ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በኮሌጁ አሰልጣኞች በአሶሳ ግብርና ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለተመዘገቡ ሴት ስልጣኞች የመጀመሪያ ምዕራፍ ስልጠናውን በንድፈ ሀሳብ ካጠናቀቁ በኋላ በተግባር የታገዘ ስልጠና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሰኔ 4/10/2016ዓ.ም የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚዩኒኬሽን።