የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች እና አሰልጣኞች እንደሀገር ለሁሉም ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የሚሰጠው የማነቃቂያ ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ከቀን 21/12/2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ አሶሳ ዩኒቨርስቲ የስልጠና ማዕከል የገቡ ሲሆን ስልጠናው ከ22/12/2016 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጷግሜ 3 የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ጊዜውን የዋጀ ወጥ አቅምና ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራትን ዓላማ ያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ሰልጣኞች ከሰልጠናው የሚያገኙት ዕውቀትና ክህሎት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን የሚወስኑበት መሆኑን በመገንዘብ በንቃት መከታተል እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *