የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ “GIZ QEP Assosa Office ” ጋር በመተባበር በቤንሳይከን ሆቴል የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ አድርጓል

የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ “GIZ QEP Assosa Office ” ጋር በመተባበር በቤንሳይከን ሆቴል የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ አድርጓል ኮሌጁ ከቤ.ጉ.ክ.መ. ስራና ክህሎት ቢሮ፣ የጅ.አይ. ዜድ አሶሳ ቅርንጫፍ ፣ የኢት/ያ ቀይ መስቀል ቤ.ጉ ቅርንጫፍ ፣ ቤ.ጉ.ክ.መ. አደጋ ስጋት የስራ አመራር ኮማሽን ግባር ቀደም ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክቱ የሚኖራቸዉን ሚና በማቀናጅት በተቋም ደረጃም የኮሌጁን ዲን ጨምሮ በፕሮጀክቱ የተካተቱ ዲፓርትመንት ተጠሪዎች እና ስራዉን የሚያስተባብሩ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካታች የአጫጭር ስልጠና ማስጀመሪያ ወርክ ሾፕ ተካሂዷል ።
በፕሮግራሙ ላይ ጅ.አይ.ዜድ ላለፉት አምስት አመታት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መስራቱ ተገልጿል ከስራዎቹ መካከል በተመረጡ አካባቢዎች ተግባር ተኮር አጫጭር ስልጠናዎችና የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራሞች ለስደተኞችን እና የአካባቢውን የማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረጉ ተገልጿል።
“GIZ QEP II inclusive vocational college IV short term training project”
ማስጀመሪያ ፕሮግራሙን በተመለከተ ገበያ ተኮር የስልጠና ዘርፎች ማለትም አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጆ፣ ኮንስትራክሽን ቴክኖሎጅ፣ ኤሌክትሪክ፣ እንጨት ስራ፣ ሆቴልና ቱሪዝም እና የብረታብረት ስራዎችን ያካተተ ሲሆን በአጠቃላይ 100 ተጠቃሚዎችን በመያዝ ከእነዚህም 50 ከአካባቢው ማህበረሰብ የተውጣጡ ሲሆን ቀሪዎቹ 50 ደግሞ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው። የስልጠና ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በግዥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማሟላት በታቀዉ ጊዜ በማቅረብ ፕሮጀክቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር እንዲሁም የታለመውን የስልጠና ግብ ለማሣካት ከባለድርሻ አካላት ጋር
በመቀናጀት መስራት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን የኮሌጁ ዲን ወ/ሮ መናህል እምራን ገልፀዋል።
21/06/2016 ዓ/ም በኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት ስራ ክፍል::
All reactions:

Melese Beyene and 20 others

All reactions:

Endris Ali, Damte Eteffa and 58 others