ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም የኮሌጁ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላትና የድፓርትመንት ሀላፊዎች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የ9ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት በዝርዝር ቀርቦ ተገምግሟል ።
ሪፓርቱ በትምርትና ስልጠና በቴክኖሎጅ ሽግግር እንዲሁም በአስተዳደር ዘረፍ በመከፋፈል የቀረበ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮች እና ወደፊት ትኩረት የሚሹ ነጥቦችንም አካቷል።
የኮሌጁ ት/ስ/ዋ/ስ/ሂ/ም/ዲን አቶ ግዛቸው በጋንፄ እንደገለፁት በሁለቱም ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር በማየት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ዉስንነቶችን በማንሳት ለቀጣይ እንደ ግብአት በመዉሰድ በቴክኖሎጅም ሆነ በስልጠናው ዘረፍ ከሌሎች ተቋማት ተሞክሮዎችኝ በመውሰድ የኮሌጁን የውስጥ ገቢ ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የቴ/አቅ/ክ/ሽ/ዋ/የስ/ም/ዲን በአቶ አብደታ ደሬሳ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል ። ላለፉት ዘጠኝ ወራት በየዘርፉ የነበሩ ውስንነቶችን በመቅረፍና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እንዲሁም በየደረጃው የሚያደርጉትን ጥረቶች በማስቀጠል የተጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት ሊወጡ እንደሚገባም አያይዘው አሳስበዋል።




