የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2014 የትምህርት ዘመን በ9 ድፓርትመንት ተቀብሎ ሲያሰለጥን የቆየውን 120 ሰልጣኞች በዛሬው ቀን አስመርቋል

(አሶሳ:ነሀሴ 25/2016 ዓ,ም)
ኮሌጁ ከተቋቋመበት ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ለ22ኛ ጊዜ እያስመረቀ ሲሆን ይህም ከደረጃ ሁለት እስከ አምስት በመደበኛና በማታ 89 ሰልጣኞችን በአጫጭር  ስልጠና ደግሞ ሶሻል ወርክ ከክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር በመሆን 31 ሰልጣኞችን በፅንሰ ሀሳብና በተግባር አሰልጥኖ በማስመረቅ ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ዜጋ ለማፍራት የበኩሉን ሚና ተወቷል::

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱ ሰላም ሸንገል ኮሌጁ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት አንጋፋ ኮሌጅ ሲሆን መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመስራት ከመደበኛ ስልጠና ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያንን እና ስደተኞችን የክህሎት ስልጠና በመስጠት የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ በማድረግ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል;;

አክለውም ኮሌጁ ተልዕኮውን ለማስፈፀም ተወዳዳሪ የሰው ሀይል በማፍራት ተቀናጅቶ መስራትና የላቀ ውጤት ማስመዝገብ አለበት በማለት ለተመራቂ ሰልጣኞች በተመረቁበት ሙያ መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ተደራጅቶ ወመስራት ለማህበረሰቡ ችግር ፈችና ለሌሎች የስራ ዕድል በመፍጠር ሀገራችንን ከድህነት ለማላቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል::

የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አቶ ተመስጌን ሀይሉ :- ተመራቂዎች ኮሌጁ ውስጥ በነበራችሁ ቆይታ በቀሰማችሁት የተግባርና የፅንሰ ሀሳብ እውቀት ተጠቅማችሁ የራሳችሁን ህይወት ከመለወጥ ባለፈ ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገር ለሌሎች የስራ ዕድል ፈጣሪ መሆን አለባችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
በመጨረሻም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሰልጣኞች ዋንጫ እና ሜዳልያ በመሸለም ምርቃቱ ተጠናቋል::

በኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Exif_JPEG_420

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *