(አሶሳ፤ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም) በኮሌጁ አመራሮች ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች በተገኙበት የ2016 በጀት ዓመት የ12 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የጥቅል ሪፖርት ግምገማ መድረክ በትናትናው ዕለት ሲካሄድ ቆይቷል::
ከትናትናው በመቀጠል:- የአመቱ ሪፖርት አፈፃፀም ላይ የኮሌጁን ሁሉንም ሰራተኞች በማሰተፍ በጥልቀት በመገምገም ያሉትን ክፍተቶች ለይቶ ለቀጣይ በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራትና ራሳቸውን በደንብ በማዘጋጀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለባቸው ተነስቷል::
ባለፉት 2016 በጀት አመት በኮሌጁ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን በጥልቀት በመገምገም እና የ2017 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ የሚሆኑ ግበዓቶችን በመሰብሰብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል
በኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት