(ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም ፣ አሶሳ ) የአሶሳ ፓሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር “የምትተክል ሀገር የሚፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ አሮሜላ ቀበሌ ተገኝተው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አከናውኗል ***
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 600 ሚለዮን የሚከናወን ሲሆን በክልል ደረጃ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 15 ሚሊዮን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ከጥዋቱ 12:00 ጀምሮ ይከናወናል ።
በዚህ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ዘመቻ ጥሪ ከዳር ለማድረስ የኮሌጁ ሰራተኞች ሌሎች ሴክተር የመንግስት መ/ቤቶች ጋር በመሆን በተሰጠው ስምሪት መሰረት በአሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ አሮሜላ ቀበሌ በተዘጋጀው የችግኝ ተከላ ስፍራ አሻራቸውን አኑረዋል ።
የችግኝ ተከላ ዘመቻ ያስፈለገበት ምክንያት በሀገራችን የደን ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ እየተመናመነ በመምጣቱ የአየር መዛባት ችግር የሚያመጣውን ጉዳት ለመከላከልና ወደነበረበት የቀደምት የደን ሽፋን ለመመለስ እንደ ሀገር የተያዘውን ዓላማ እውን ለማድረግ ነው።
ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው እንደ ሀገር መነቃቃትን የፈጠረ ፣ በታሪክ ዘመን ዜጎች የራሳቸውን አሻራ እንዲጥሉ ዕድል የፈጠረና እንደ ባህልም እየሆነ መምጣቱን ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ለመረዳት ተችሏል ።
በመጨረሻም ከዚህን በፊት የተተከሉ ችግኞች አድገው ለአከባቢው ውብ ገፅታ የፈጠሩ በመሆናቸው ለመጪው ዘመን ሞራል የፈጠረ በመሆኑ የሚተከሉ ችግኞች በጥንቃቄ ተጠብቀው በእንክብካቤ ማደግ አንዳለባቸውና ቀጣይነት እንደሚኖረው አስተባባሪዎችገልፀዋል ።





